የዲላ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት - የዲጂታል አገልግሎት
የዲላ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ዲጂታል አገልግሎት
የዲላ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለደንበኞች ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል ሲስተም አገልግሎት ዘርግቷል።
የዲጂታል ሲስተሙ የድርጅቱን የሥራ አሠራር ከወረቀት አጠቃቀም ወደ ዲጂታል አሠራር በማሸጋገር የደንበኞችን መረጃ በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር፣ የአገልግሎት ሂደቶችን ለማቀላጠፍ፣ የአገልግሎት ጊዜን ለመቀነስ እና የመረጃ ተደራሽነትን ለማሻሻል ያግዛል።
በሲስተሙ አማካኝነት ድርጅቱ የደንበኞችን መረጃና የአገልግሎት ሂደቶች በዲጂታል መልኩ ማስተዳደር፣ የደንበኞችን ጥያቄና ቅሬታ መቀበልና መከታተል፣ የአገልግሎት ሂደቶችን መቆጣጠር እና ተገቢውን መረጃ በፍጥነት ማግኘት ይችላል።
በተጨማሪም ድርጅቱ ነፃ የስልክ ጥሪ 7697፣ የድር ሳይት እና SMS አገልግሎቶችን በመጠቀም ከደንበኞች ጋር የሚደረገውን የመረጃ ልውውጥ አቀላጥፏል።
የዲጂታል አገልግሎቱ ዋና ዓላማ ደንበኞች አገልግሎት ለማግኘት የሚያሳልፉትን ጊዜ መቀነስ፣ የሥራ ሂደቶችን ማቀላጠፍ፣ የመረጃ አያያዝን ማሻሻል፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማጠናከር እና የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ ነው።
ስርዓቱ የድርጅቱን የውስጥ አሠራር በማዘመን የሥራ ቅልጥፍናን ለማሳደግና የውኃና ፍሳሽ አገልግሎቱን ለከተማው ነዋሪዎች በተሻለ ደረጃ ለማቅረብ የሚያግዝ ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት መሠረተ ልማት ነው።