የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት

የመረጃ ልውውጥ በማቀላጠፍና የመንግሥት ተግባራት በማስተዋወቅ

አገልግሎቱ የከተማ አስተዳደርና ሕዝብ መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ በማቀላጠፍና የመንግሥትን ተግባራት በማስተዋወቅ ረገድ ያተኩራል። በዚህም መሠረት፡- -

  • የከተማ አስተዳደር ፖሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ስኬቶችን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች (ሬዲዮ፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ጋዜጣ) ለሕዝብ ያደርሳል፤ - የከተማ ኃላፊዎች ሕዝብን በቀጥታ የሚገናኙበትን መድረኮች (ንግግር፣ ውይይት) በማዘጋጀት ድጋፍ ያደርጋል፤ 
  • በከተማ ውስጥ የሚከሰቱ ወሳኝ ክስተቶችንና የልማት እንቅስቃሴዎችን በፎቶና በቪዲዮ በመቅረጽ ለዘመናት የሚቆይ መረጃ ያከማቻል፤ - በከተማ ውስጥ የሚሠሩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት (ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች) በሕግ መሠረት እንዲሠሩ በመቆጣጠር ከፍትሕ መምሪያ ጋር ይሠራል፤
  • በከተማ ውስጥ በሚዲያ ዙሪያ ለሚነሱ የሐሰት ወሬዎችና አወንታዊ ያልሆኑ ዘገባዎች የማስተባበያ መረጃ በማዘጋጀት ግልጽነትን ይፈጥራል፤ - በከተማ መምሪያዎች ውስጥ የሚሠሩ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለማሻሻል ድጋፍ ያደርጋል።