የቱሪዝም መምሪያ
የዲላ ከተማን በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ
መምሪያው የዲላ ከተማን በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ይተጋል። በዚህም መሠረት፡- (ሀ) የከተማን የቱሪዝም ሀብቶች (ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ) በመለየት ካርታ በማዘጋጀትና በማስተዋወቅ ለቱሪስቶች ማራኪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ (ለ) ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር ወደ ቱሪስት መዳረሻዎች የሚወስዱ መንገዶችና መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ (ሐ) በከተማ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የሆቴል፣ የሎጅና ለሌሎች የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ በመስጠት አገልግሎታቸው ጥራት ያለው እንዲሆን ይቆጣጠራል፤ (መ) የማኅበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምን በማበረታታት የአካባቢው ሕዝብ በቱሪዝም ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርጋል፤ (ሠ) የቱሪስት መስህቦችን ንጽህናና ጥበቃ በማስፈን ዘላቂ ቱሪዝም እንዲዳብር ይሠራል፤ (ረ) በባህልና ስፖርት መምሪያ አማካኝነት የተጠበቁ ባህላዊ ቅርሶችንና ወጎችን ለቱሪዝም ምርትነት በማዘጋጀት ረገድ ያግዛል።
የቱሪዝም መምሪያ
/departments/tourism