የትራንስፖርትና መንገድ ልማትና አስተዳደር መምሪያ
በከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎትን በማስተባበርና የመንገድ መሠረተ ልማትን በማስፋፋትና በመንከባከብ
መምሪያው በከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎትን በማስተባበርና የመንገድ መሠረተ ልማትን በማስፋፋትና በመንከባከብ ረገድ ቁልፍ ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት፡-
- የከተማዉን መንገዶች አውታር በማስፋፋትና በማሻሻል ለሁሉም ማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ይሠራል፤
- የከተማ መንገዶችን በየወቅቱ በመቃኘት የጥገናና የዕድሳት ሥራዎችን በማስተባበር መንገዶች አገልግሎት መስጠታቸውን ያረጋግጣል፤
- በከተማ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች (አውቶቡስ፣ ታክሲ) ፈቃድ በመስጠት፣ የሚከፍሉትን ታሪፍ በመቆጣጠርና የትራንስፖርት ደህንነትን በማረጋገጥ አገልግሎቱን ይቆጣጠራል፤
- የመንገድ ደህንነት ንቅናቄዎችን በማዘጋጀትና የትራፊክ ሕጎችን በማስከበር የመንገድ አደጋዎችን ለመቀነስ ከሰላምና ጸጥታ መምሪያ ጋር በመተባበር ይሠራል፤
- ከፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በከተማ ውስጥ የሚገኙ የፌዴራል መንገዶች ግንባታና ጥገና ሥራዎችን ይከታተላል፤
- በከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትንና የተሸከርካሪ ጥገና ጋራጆችን በመቆጣጠር የሚሰጠው አገልግሎት ጥራት ያለው እንዲሆን ያደርጋል።