ዲላ ከተማ
የዲላ ከተማ ታሪካዊ ዳራ
ዲላ ከተማ በ1904 ዓ.ም ስትቆረቆር በ1942 ዓ.ም በማዘጋጃ ቤት መመራት ጀመረች፡፡ ቀድሞ የነበራት የቆዳ ስፋት 2 ሺህ 141.21 ሄክታር የነበረ ሲሆን አዲስ በተሰራው የዕድገት ፕላን መሰረት 4 የገጠር ቀበሌያትን በማካተት አሁን ያላት የቆዳ ስፋት 5 ሺህ 138 ሄክታርነው፡፡
አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 215 ሺህ 870 የከተማ ነዋሪዎች በ3 ቀበሌያት 15 ቀጠናዎች ያላት ሲሆን የዲላ ከተማን በሰሜን የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ የዲላ ዙሪያ ወረዳ በምዕራብ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያዋስናታል፡፡
ከተማዋ ከባህር ጠለል በላይ 1 ሺህ 600 ሜትር
አስትሮኖሚካል አቀማመጧም 6.4 ድግሪ ላቲቲዩድና 38.10 ድግሪ ፋራናይት ሲሆን አመታዊ የሙቀት መጠን 20 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ በአማካይ ሆኖ አመታዊ የዝናብ መጠን 1ሺህ 215 ሚሊ ሊትር ነው፡፡
ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች መካከል እንዷ ስትሆን አሁን ላይ የክልሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ክላስተርና የክልል መቀመጫ እንዲሁም የዲላ ከተማ ዋና ከተማ ሆና በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች በአብሮነት ይኖሩባታል፡፡
ዲላ በ1904 ዓ.ም ስትቆረቆር የዛሬውን የከተማነት ቅርጽ ከመያዟ ቀደም ብሎ ከሸዋ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በሚደረገው የንግድ ልውውጥ መሸጋገሪያ መስመር በመሆን በሀገረ ኢኮኖሚ አዎንታዊ አሻራ በመጣል ታሪካዊ ድርሻዋን ተወጥታለች፡፡
ያኔ አብዛኛው የከተማዋ አከባቢ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነና የአራዊት መኖሪያ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ የኢትዮ ቴሌ ኮሚኒኬሽን ተቋም በሚገኝበት ስፍራ ጥቂት ጎጆዎች በመቀለስ ነበር ከተሜነቷ የተባለው፡፡
በወቅቱ የአከባቢው ገዢና የከተማዋ ቆርቋሪ መሆናቸው የሚነገርላቸው ባራምባራስ በደቻ ኡዶ መኖሪያቸውን የአሁኑ ቴሌ ኮሚኬሽን ተቋም
በተገነባበት ስፍራ ቤት ሰርተው አከባቢውን ማስተዳደር በጀመሩበት ወቅት ሌሎች ሰዎችም በዚያው አካባቢ መኖሪያቸውን ቀልስው መክተማቸውን ታሪክ ያስረዳል፡፡ መኖር ጀመሩ፡፡
ከተማዋ ከ1920 ዓ.ም ጀምሮ የቡና ግብይት ማዕከልነቷ እየጎላ ከግብይት ማዕከልነቷ ጋር ተያይዞም የባሪያ ንግድ እና ህገ ወጥ መሳሪያ መቆጣጠሪያ ጉሙሩክ በመቌቌሙ የነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ የባለስልጣናት ጉብኝት እየተጠናከረባት መጣ፡፡
ከተማዋ ዛሬም የኢትዮ ኬንያ አስፓልት መንገድ አቌርጧት የሚያልፍ መሆኑ ለንግድ ማዕከልነቷ መጠናከር የራሱን አስተዋጽዖ ያበረከተ ከመሆኑም በላይ በአከባቢው ያሉትን የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን ሆነ ደቡብ ኦሞ ኮንሶ እና ሌሎች ስፍራዎችን የሚጎበኙ ቱሪስቶችን በማረፊያነት እየተገለገሉባት ትገኛለች፡፡
ዛሬም በዲላ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችና መልክዓ ምድር በአለም የትምህርት የባህልና ሳይንስ ድርጅት (UNESCO) መመዝገብ ተከትሎ ከተማዋን የብዙኃን መኖሪያና ማረፊያ ነግዶ ማትረፊያና ሓብት ማፍሪያ ከተማ ሆናለች፡፡
ፕላን
ዲላ ከተማ በክልሉ የፕላን ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም መረጃ መሠረት የከተማው ህዝብ ብዛት 215,870 ሲሆን፣ የዓመታዊ የዕድገት መጠን /annual growth rate/ 4.8 ከመቶ ነው።
ዲላ ከተማ የኢትዮ-ኬኒያ ዋና መተላለፊያ መንገድ ላይ ስትገኝ የሶስት ማእዘን ቅርጽ ሲኖራት በአረንጓዴ ደን የተሸፈነች በቡና እና ፍራፍሬ ምርት የሚትታወቅ ከተማ ነች፡፡
1600 ከባህር ጠለል ከፍታ ላይ የሚትገኘዋ ከተማዋ፤ሞቃታማ ስትሆን ዓመታዊ የሙቀት መጠኗ 20 ዲግሪ ሴሊሺየስ አመታዊ የዝናብ መጠን 1215 ሚ.ሜ ነው፡፡
በከተማው የ10 ዓመት መዋቅራዊ ፕላን መሠረት ከ2016 እስከ 2026 ዓ.ም የከተማ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 5,138 ሄክታር ነው፡፡
ዲላ ከተማ በምዕራብ ከኦሮሚያ ጋር በሰሜን ከሲዳማ ክልል ጋር ስትዋሰን በሶስት ወንዞች የተከበበች ስትሆን ለገዳራ ወንዝ በሰሜን፤ዋለሜ በምዕራብ ወንዝ እንዲሁም ጪጩ ወንዝ በደቡብ ያዋሰኗቷል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገችና እየሰፋች የመጣቸው የዲላ ከተማ የሕዝቧ ብዛት ከ135,000-170,000 ሲገመት ወንድ 51% ሴት 49% ይይዛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ከሚገኙ ከተሞች ለገጠርና ከተማ ትስስር ምሳሌ መሆኗ የሚነገርላት የዲላ ከተማ በገጠር የሚስተዋለው የእንሰት ቡናና ዛፍ ቁርኝነት በከተማዋ ይታያል፡፡
ለዚህም የመንገድና የመሰረተ ልማት አውታሮች በአዳዲሶቹ የከተማዋ ማስፋፍያ አከባቢዎችና ስፍራዎች ወቅቱን ጠብቆ ደረጃውን በጠበቀ የፕላን ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ራዕይ እና ተልዕኮ
ራዕይ
ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ የብልጽግና እና የዘላቂ ዕድገት ምልክት፤ እንዲሁም የዕድል፣ የአካታችነት እና የላቀ የከተማ ኑሮ ጥራት የሚንፀባረቅባት ከተማ ሆና ማየት።
ተልዕኮ
የዲላን ገጽታ ለመገንባት፣ ኢንቨስትመንትን እና ትብብርን ለማሳደግ የአካባቢ፣ የአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን ማጠናከር።
በሁሉም የህዝብ አገልግሎቶች ፍትሃዊነትን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈን።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ፣ የከተማ ልማት አገልግሎቶችን ለዜጎች መስጠት።