እንደ ሐገር በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ጭምር እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ቀድሞ የነበሩ ከተሞችን ገፅታ በመቀየር አዲስ ገፅታን በማላበስ ከተሞችን ውብ ማራኪና ተመራጭ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
የኮሪደር ልማት አዲስ ኢንሼቲቭ እንደመሆኑ በአተገባበር ወቅት ዉስን ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም አሁን ላይ በመንግስት ብቻ ሳይሆን በሕብረተሰቡ ተሳትፎም ጭምር ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል
ይህ አዲስ ከተማ ፈጣሪ ኢንሼቲቭዲላ ከተማን ለነዋሪዎች ለኑሮ ምቹ እንዲሁም ተወዳደሪ ከተማ ለማድረግ እየተተገበሩ ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች የመንገድ ኮሪደር ልማት መከወን ነው።
ባለፉት ዓመታት በከተማችን የመንገድ ኮሪደር ልማት የሚከወንባቸው በቁጥር 8 ዋና ዋና ኮሪደሮችን 18 ኪ.ሜትር በላይ በመለየት የፕላን ማስጠበቅ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡
ለኮሪደር ልማት ሥራ የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የከተማ ፕላን የማስጠበቅ ሥራ ሲሆን በዚህመ ረገድ በከተማው ነዋሪ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም በየደረጃው ባሉ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ሥራ ከ19.2 ኪሎሜትር በላይ ፕላን የማስጠበቅ ተግባር ተከናውኗል፡፡
የከተማው ነዎሪዎች በፕላን ማስጠበቅ ተግባሩ ባደረጉት ንቁ ተሳትፎ ከመንግሥት ሊወጣ የነበረውን 654 ሚሊዮን ብር ማዳን የተቻለ ሲሆን 517 ቤቶችን በማፍረስ የከተማ ፕላን ማሰጠበቅ ተግባር በማከናወን ለቀጣይ የመንገድ ኮሪደር ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡
ከአዲስ አበባ ሞጆ ኢትዮ ኬኒያ የሚዘልቀው አስፋልት መንገድ አቋርጧት የሚያልፈው የዲላ ከተማመግቢያበር ላይ እጅግ ሳቢና ማራኪ የመግቢያ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ በከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በኮሪደር ልማት በመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት 16 ሺህ 700ካሬሜትርተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በተመሳሳይ 8.4 Km እግረኛመንገድ ተጠናቋል፡፡
በቁጥር 5 እስናክሀውስግንባታ ተጠናቅቆ በእዚሁአከባቢ 20 ማረፊያ መቀመጫዎች ተዘጋጅተ ሕብረተሰቡ አረፍ ብሎ ነፋሻ አየር እንዲቀበልና ራሱን እንዲያዝናና አስተዋኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡
በከተማው የሚገኙ 2 አደባባዮችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማልማት እና የማስዋብ ሥራ ተሰርቶ 4ኪ.ሜ የመንገድ መብራት ማስዋብ ሥራ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡.
የኮሪደር ልማት ከተማን እንደ አዲስ ከነፍጠር ባሻገር ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል በመፍጠርም አበርክቶቱ ከፍተኛ ሆኖ በዲላ ለ1ሺህ 205 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
የዲላ ከተማ የኮሪደር ልማትን በማስቀጠል በከተማዋ ክልል ዋና ዋና መንገዶች ላይና አደባባዮች ብሎም ሰው ሰራሽ ሐይቅም ጭምር በመስራት አዲስ ከተማ የመፍጠሩ ተግባር ከነዋሪዎቻችን ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡