የፍትሕ መምሪያ
በከተማ ውስጥ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ የዜጎችን መብት በመጠበቅና ፍትህ በማስፈን
መምሪያው በከተማ ውስጥ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ የዜጎችን መብት በመጠበቅና ፍትህ በማስፈን ረገድ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታል። በዚህም መሠረት፡- (ሀ) የከተማ አስተዳደርና የበታች አካላት በሚያወጡት ደንብና መመሪያ ሕገ-መንግሥታዊነት ላይ የሕግ አስተያየት በመስጠት ዋና አማካሪ ሆኖ ያገለግላል፤ (ለ) በከተማ ውስጥ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ክስ በማቅረብና በመከራከር የሕዝብ ዐቃቤ ሕግነት ሚናውን ይወጣል፤ (ሐ) የሴቶች፣ ሕጻናትና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ችግረኞች ነፃ የሕግ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ (መ) በከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችንና የንግድ ማኅበራትን በመመዝገብ ሕጋዊ እውቅና ይሰጣል፤ (ሠ) የሕግ ትምህርትና ንቃተ-ሕግ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ማኅበረሰቡ መብቱንና ግዴታውን እንዲያውቅ ያደርጋል፤ (ረ) በከተማ ውስጥ የሚገኙ ማረሚያ ቤቶችን በመቆጣጠር የእስረኞች መብት መከበሩንና የማረሚያ ተቋማት በአግባቡ እየተመሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
የፍትሕ መምሪያ
/departments/justice