ይጎብኙ
ቡካር ዋሻ
ከዲላ ከተማ 2 ኪ.ሜበከተማዉ ከሚገኙ ቀበሌያት መካከል በሐሮሬሳ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ዋሻ ነው። በትላልቅ ድንጋዮች ስር የሚገኝ ሲሆን ልዩ የሆነ የሶፍሁመር ዓይነት ቅርጽ ያለው መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ያለዉ ነዉ። ለፎቶ አገልግሎት ምቹ ከመሆኑም በላይ አስፋልት መንገድ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ ነዉ።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ጪጩ ባህላዊ ሸንጎ
ከዲላ ከተማ 5 ኪ.ሜበጪጩ ቀበሌ የሚገኝ ባህላዊ ቱሪስት መስህብ ነው። ይህ ቦታ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓትን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል ልዩ ባህላዊ ይዘት ያለው ነው። አስፋልት መንገድ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ሌሎች የቱሪስት መስህቦች በአቅራቢያው ይገኛሉ።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ቡካር የድንጋይ ንርብራብ
ከከተማ 2 ኪ.ሜበሐሮሬሳ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ቱሪስት መስህብ ነው። ማራኪ የመልክዓ-ምድር አቀማመጥ ያለው ነው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ቡካር ጥቅጥቅ ደን
ከዲላ ከተማ 2 ኪ.ሜበሐሮሬሳ ቀበሌ የሚገኝ ጥቅጥቅ ያለ ደን ነው። ተፈጥሯዊ መስህብ ሲሆን አስፋልት መንገድ በአቅራቢያው ስላለ ተደራሽ ነው። በዙሪያው ካሉ ሌሎች ቦታዎች ጋር ተያይዞ ለማልማት ምቹ ነው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ቦታንካል ጋርደን
ከዲላ ከተማ 1.5 ኪ.ሜ
በሴሳ አዳያአ ቀበሌ የሚገኝ ሰው ሰራሽ መናፈሻ (ፓርክ) ነው። ዘና ለማለትና ፎቶ ለማንሳት ምቹ የሆነ ማራኪ አካባቢ ነው። መሠረተ ልማት በአቅራቢያው ያለ ሲሆን ከግል ዘርፍ ጋር በመተባበር ለማልማት የሚያስችል አመቺነት አለው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ሳሮን ሎጅ ተራራ
ከዲላ ከተማ 1.5 ኪ.ሜ
በሴሳ አዳያአ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ተራራ ነው። ለአይን የሚማርክ መልክዓ-ምድር ያለው ሲሆን አስፋልት መንገድ በአቅራቢያው አለው። በአካባቢው የቱሪም ፋሲሊቲዎች በመኖራቸው ለኢንቨስትመንት ምቹ ነው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ቱሉ ተራራ ደን
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሴሳ ጎላ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ደን በተራራ ላይ ነው። ማራኪ የተፈጥሮ ሙቀት አለው። ዋና መንገድ በአቅራቢያው በመኖሩ ተደራሽ ነው። የአካባቢው ማህበረሰብ በቱሪዝም እንቅስቃሴ የመሳተፍ ፍላጎት አለው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ባሹ ተራራ
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሴሳ ጎላ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ተራራ ነው። ማራኪ መልክዓ-ምድር ያለው ሲሆን መሰረተ ልማት በአቅራቢያው ይገኛል። እንደ መሰረተ ልማት አውታሮች ለቱሪዝም እንደ ግብአት ሊያገለግሉ ይችላሉ።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
አዋላ ፏፏቴ
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሜትሌ ሶሶታ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ፏፏቴ ነው። በውበቱ የሚማርክ ሲሆን ለፎቶ አገልግሎት ምቹ ነው። አስፋልት መንገድ አቅራቢያ ስላለ በቀላሉ መድረስ ይቻላል።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
አንዲዳ ጸበል
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሴሳ አንድዳ ቀበሌ የሚገኝ የፍል ውሃ ጸበል (ሙቅ ምንጭ) ነው። ተፈጥሯዊ መስህብ ሲሆን ለጎብኚዎች ዘና ለማለት እና መዝናናት የሚያስችል ነው። በአስፋልት መንገድ አቅራቢያ ይገኛል።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ጋንሻሞ አዋላ ፓርክ
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሜትሌ ሶሶታ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ፓርክ ነው። ማራኪ የሆነ መልክዓ-ምድር ያለው ሲሆን መንገድ በአቅራቢያው አለው። ከሌሎች የቱሪስት መስህቦች ጋር ተያይዞ ለማልማት ይመቻል።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ባዱቂያ ጨብቻ ቋጥኝ
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሜትሌ ሶሶታ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ቋጥኝ ነው። ለአይን የሚማርክ ውበት ያለው ሲሆን አስፋልት መንገድ በአቅራቢያው አለው። የአካባቢው ማህበረሰብ ከቱሪዝም ልማት ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ውስጥ ደዌ ፈዋሽ ቆሜ ዳላጭ ጎዳ ውሃ
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሜትሌ ሶሶታ ቀበሌ የሚገኝ ውሃ ጸበል ነው። በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ለውስጥ ደዌ (ለሆድ ሕመም) ፈውስ እንደሚሆን ይታመናል። በአስፋልት መንገድ አቅራቢያ ስለሚገኝ ተደራሽ ነው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ቆሜ ዳላጭ ጎዳ የአንብው ውሃ
ከዲላ ከተማ 3.5 ኪ.ሜ
በሜትሌ ሶሶታ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ውሃ ነው። ለአይን የሚማርክ መልክዓ-ምድር ያለው ሲሆን በውሃው ባህሪ የተለየ ነው። የአካባቢው ማህበረሰብ የቱሪዝም እንቅስቃሴ የመፍጠር ፍላጎት አለው።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ቾንቤ ፍል ውሃ ጸበል
ከዲላ ከተማ 1.5 ኪ.ሜ
በሴሳ አዳያአ ቀበሌ የሚገኝ የፍል ውሃ ጸበል (ሙቅ ምንጭ) ነው። ለፈውስና ለመዝናናት የሚያገለግል ነው። በአስፋልት መንገድ አቅራቢያ ይገኛል።
ይምጡና ይጎብኙ
ይጎብኙ
ሳቤህ ተንጠልጣይ ድልድይ
ከዲላ ከተማ 1.5 ኪ.ሜ
በሴሳ አዳያአ ቀበሌ የሚገኝ ድልድይ ሲሆን ለእግረኛ ተንጠልጥሎ የሚያልፍበት ነው። በአካባቢው ያለው መልክዓ-ምድር ለጎብኚዎች ልዩ ልምድ ይፈጥራል። አስፋልት መንገድ በአቅራቢያው አለ።
ይምጡና ይጎብኙ