የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት

እንኳን በሰላም መጡ ዲላ ከተማ አስተዳደር

ዲላ ከተማ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የግብርና ክላስተር መቀመጫ የሆነች እንግዳ ተቀባይ እና ውብ ናት።

አረንጓዴዋ ከተማ

215,870
ህዝብ
1,550
ከባህር ጠለል በላይ
20
ሙቀት
4.8%
አመታዊ እድገት

እንኳን ወደ ዲላ ከተማ በደህና መጡ

ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ደማቅና እንግዳ ተቀባይ ከተማ ስትሆን፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የግብርና ክላስተር መቀመጫ በመሆን በማገልግል ላይ ትገኛለች።

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በግምት 360 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአዲስ አበባ-ሐዋሳ-ሞያሌ ዋና መንገድ ላይ የምትገኘው ዲላ ለኑሮ፣ ለንግድ እና ለአዳዲስ እሳቤዎች አመች ከተማ ናት። ዲላ በመሠረተ ልማት፣ በሕዝብ አገልግሎቶች፣ በከተማ ልማት ዘርፎች እና በኮሊደር ልማት እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ በፍጥነት በማደግ ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። በተለይ ከተማዋ ለዓለም ገበያ በሚቀርበው እና ዓለም አቀፍ ዝና ባለው ኦርጋኒክ (ተፈጥሯዊ) የይርጋጨፌ ቡና በስፋት ትታወቃለች። 

 የከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች፣ ለጎብኝዎች እና ለልማት አጋሮች ምቹ እና ለኢንቨስትመንት ተስማሚ የሆነ አካባቢን በመፍጠር ረገድ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አረንጓዴ እና የበለፀገች ከተማ ለመገንባት በትጋት እየሰራ ይገኛል።

View Full Size

ራዕይ እና ተልዕኮ

✓

ራዕይ

ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ የብልጽግና እና የዘላቂ ዕድገት ምልክት፤ እንዲሁም የዕድል፣ የአካታችነት እና የላቀ የከተማ ኑሮ ጥራት የሚንፀባረቅባት ከተማ ሆና ማየት።

✓

ተልዕኮ

1

የዲላን ገጽታ ለመገንባት፣ ኢንቨስትመንትን እና ትብብርን ለማሳደግ የአካባቢ፣ የአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን ማጠናከር።

2

በሁሉም የህዝብ አገልግሎቶች ፍትሃዊነትን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈን።

3

ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ፣ የከተማ ልማት አገልግሎቶችን ለዜጎች መስጠት።

የመሪዎች መልዕክቶች

የከንቲባ መልዕክት

ዶ/ር መስፍን ደምሴ

የዲላ ከተማ ከንቲባ

ዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ረጂዮ ፖሊሲ ከተሞች መካከል እንዷ ሰትሆን አሁን ላይ የክልሉ ግብርና ክላስተር ማዕከል የበርካታ ብሄር፤ብሄረሰቦች በአብሮነት የምኖሩባት ከተማ ነች። ከተማችን የመደመር መንግሥት ለከተሞች ዕድገት የሰጠው ትኩረት መነሻ የከተማችን ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ እና ለነዋሪዎች ምቹ የቱሪስቶች መዳረሻ እንዲሆኑ እና ፀጋቸውን ለይተው እንዲያድጉ የተወሰደው እርምጃም ውጤት እያሳየ ይገኛል። በተለይም የኮሪደር ልማት ሥራው ከተማውን በማዘመን ለኑሮ ምቹ፣ጽዱ እና ውብ እንዲሆኑ በማድረግ የከተማችንን ገጽታ የሚቀይር መሰረት በመሆን በተለይም ከተሞችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና አገልግሎቶችን ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል። በገጠር እና በከተማ ያለውን የዘመናዊ አኗኗር ልዩነት በማጥበብ እንዲሁም ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንዲቻል ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉም። ከለውጡ በፊት ለከተሞች እድገት ትኩረት ባለመሰጠቱ፣ከተሞች በሚገባቸው መጠን እንዳያድጉ ምክንያት ሆነው የቆየው ቢሆንም ከተሞች የተለያዩ ማንነቶች፣እሳቤዎች፣ ዕውቀት፣ካፒታል እና ሀብት የሚንሸራሸሩባቸው መሆን ስላሉባቸው የመደመር መንግሥት ከተሞች ለሁሉም ዜጋ ምቹ መኖሪያ መሆን አለባቸው የሚል እሳቤን ይዞ የመጣውን እሳቤ በጋራ እውን በማድረግ ላይ የምንገኝና ስልጡን ከተማ (ስማርት ሲቲን) ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ከተሞች ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በትኩረትም እየተሰራ ስሆን ዲላ ከተማ አረንጓዴያማ ቦታዎችን በማልማት እና ምቹ መናፈሻዎችን እንዲሁም ከተማን የሚመጥኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተሰራ ይገኛል፡፡ ውብ ከተሞች የሰው ልጆች የሥራ ውጤቶች በመሆናቸው መልካም ነገር ከሠራን ጥሩ፤ ለነዋሪው ምቹ እና የዘመኑ ከተሞችን ለማየትና ለማሳየት የበለጠ ጥረቶች ይቀጥላሉ። አመሰግናለሁ!

የመሪዎች መልዕክቶች

መልዕክት

አቶ መንግስቱ ተክሌ

የዲላ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ

ጽኑ አንድነት ለተከታታይ ድልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና የተከበራችሁ የከተማችን፣የሀገራችን ህዝቦች፣የአካባቢያችን ነዋሪዎችና የልማት አጋሮቻችን፤ ኢትዮጵያ በጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ትልቁ አቅማችን አንድነታችን ነው። ፓርቲያችን ብልጽግና ይፋ ያደረገው የ"ስንዴ ነዶ" ማንፌስቶ፣የተበታተነ ጉልበታችንን አስተሳስረን፣የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን አልምተንና ምርታማነታችንን አሳድገን ራሳችንን በራሳችን ለመቻል የገባነው ታላቅ ቃል ኪዳን ነው። መንግሥታችን በየደረጃው የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች በጽናት እየተጋፈጠ የህዝቡን ደህንነትና ልማት የማረጋገጥ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። ይህ ድህረ-ገጽ የለውጥ ጉዟችንን የምናጋራበት ግልጽነትን የምናሰፍንበትና የህዝባችንን ድምጽ የምንሰማበት መድረክ ነው። የ"ስንዴ ነዶው" ጥንካሬ በእያንዳንዳችን ትጋት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለሀገር ግንባታው በንቃት እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ አጋጣሚ በመቀየር፣ ኢትዮጵያን የብልጽግና ማማ ላይ እናወጣታለን! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

ቀጥታ ስርጭት

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

የከተማውን ወቅታዊ ማስታወቂያዎች፣ ፕሮጀክቶች እና የህዝብ መረጃዎች በቀጥታ ይከታተሉ።

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከ17 ሰዓት በፊት
Facebook post image 1 Facebook post image 2 Facebook post image 3
Facebook post image 4
+8

"የጌዴኦ ዞን የኢሬቻ በዓል የፍቅር ስጦታ ለአባጋዳዎች አበረከቱ ‎ ‎(ዲላ መስከረም 23/2019 ዓ/ም) የጌዴኦን ዞን የወከሉ ልዑካን ቡድን በኢሬቻ በዓል በመታደም ከወንድም ኦሮሞ ህዝብ ጋር ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አክብሯል። ‎ ‎ዞኑን የወከሉ ልዑካን ቡድን ለአባጋዳ ጃርሳ ጡጎ እና ለአባጋዳ ኤብሳ የቡሉኮ ስጦታ አበርክቷል። ‎ ‎ስጦታውን የተረከቡት አባጋዳዎችም ዞኑን በኦሮሞ ህዝብ ስም አመስግነዋል። ‎ዘገባው የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው።"

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከ22 ሰዓት በፊት
Facebook post image 1 Facebook post image 2 Facebook post image 3
Facebook post image 4
+6

"የጌዴኦ ዞን ሉዑካን ቡድን የ '‘ሆረ ፊንፊኔ" ኢሬቻ በዓል ላይ ለመታደም ወደ ስፍራው አቅንቷል ‎ ‎(ዲላ መስከረም 23/2019 ዓ/ም) የዞን አስተዳደር የባህል መሪ በአባ ገዳ ተወካይ ሐይቻዎች "ሆረ ፊንፊኔ" ኢሬቻ በዓል ላይ ለመታደም ወደ ስፍራ አቅንተዋል ። ‎ ‎የገዳ ሥርዓት አንዱ አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ ባህል እምነትና ማንነት ትልቅ ቦታ ያለው በአንድነትና በፍቅር በልዩ ድምቀት የሚከበር ታላቅ የምስጋና በዓል ነው፡፡ ‎ ‎ሁለቱ ወንድም ህዝብ ለዘመናት በአባ ገዳ ስርዓት በመተሳሰር ለሀገር ግንባታ እና ለልማት አብሮ የኖሩ ህዝቦች ናቸው ። ‎ ‎@የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት! ‎"

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከ1 ቀን በፊት
Facebook post image 1 Facebook post image 2 Facebook post image 3
Facebook post image 4
+8

"ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ከክልሉ አስፈጻሚ አካላት ጋር በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ መከሩ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ በዛሬው ዕለት የተካሄደውን የክልሉ የመንግስት ምስረታ ተከትሎ፤ ከክልሉ አስተባባሪና አስፈጻሚ አካላት ጋር በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ በመምከር የስራ ስምሪት ሰጥተዋል፡፡ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፡- በዛሬው የምስረታ ጉባኤ ከክልሉ ሕዝብ፤ ከፓርቲና መንግስት የተሰጠን ከፍተኛ ኃላፊነት ህዝብን በቅንነት የማገልገል ታሪካዊ ዕድል መሆኑን በውል በመገንዘብ፤ የተሰጠንን ዕድል በጥንቃቄ ይዞ ኃላፊነትን በሙሉ አቅም በመወጣት ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ የተሻለች ሀገር ለትውልድ ለማሻገር አቅዶ የተነሳ ፓርቲና መንግስት አመራሮች ነን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ አመራሩ ሙሉ ትኩረቱን ሥራ ላይ በማድረግ ለለውጥ መትጋት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ በዚህ ረገድ ባለፉ ጊዜያት በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶች ዘላቂነትን በማረጋገጥ እንዲሁም ለላቀ ውጤት በትኩረት በመስራት ለሀገራዊና ክልላዊ የሰላምና የብልፅግና ትልም ስኬት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ጠንካራ አመራር ከትላንት ወረትን አካብቶ፤ ዛሬን ለነገ አቅዶ የሚሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ አመራሩ ከመቸውም ጊዜ በላይ የተሟላ የአመራር ብቃትንና ብዝኃ ታታሪነትን ተላብሶ የሚጠበቅበትን የመሪነት ሚና በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በተለይ ክልሉ ያለውን ሰፊ ፀጋ በአግባቡ በመጠቀም የህዝብ አዳጊ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ መትጋት የሚገባ መሆኑንም ጠቅሰው፤ ለዚህ አመራሩ ሥራዎችን በጠንካራ ተቋማዊ ማዕቀፍ፤ በጥብቅ ዲስፒሊን መምራት እንደሚገባው አስምረዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ለስራዎች ውጤታማነት ከአመራሩ የሚጠበቁ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል፡- * አመራሩ የፓርቲ ዲሲፕሊንን የጠበቀ፤ በመደመር ዕሳቤ የሚመራ፤ የብልፅግና መርህ ላይ የቆመ መሆን ይኖርበታል - በዚህ ረገድ ግንኙነቱን በወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት ላይ በመመስረት የተግባርና የአመለካከት አንድነቱን ጠብቆ በኅብረትና በትብብር መስራት ይገባዋል፤ * አመራሩ በተግባሩም ሆነ በምግባሩ አራአያ መሆን ይገባዋል - ወደ ብልጽግና የሚደረግ ጉዞን የሚመራ አመራር የሚለፋና የሚተጋ፤ በስራው ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት የሚቀይር እንዲሁም በምግባሩ ወንድማማችነትን የሚተከል ልሆን ይገባዋል፤ * የልማት እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር -በተለይ እንደ ሀገር በወጥነት ሊሳኩ የሚገቡ ሀገራዊ የልማት ኢንሼቲቮችን - የሌማት ትሩፋት፣ የግብራና ትራንስፎርሜሽንን የማረጋገጥና ግብርናን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ መካናይዜሽን ላይ ማተኮር፣ የገጠርና የከተማ ኮሪደር ልማት ስራዎች እንዲሁም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋትና ጠንካራ ተቋም የመገንባት ተግባራት፤ *በተመሳሳይ በኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ ያሉ አቅሞችን አሟጦ መጠቀም፤ የኢንዳስትሪና አግሮፕሮሰሲንግ፤ የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት፤ የትምህርት ዘርፍ ስራዎች እንዲሁም ገቢን የማሳደግ ተግባራትን በትኩረት መስራት፤ * ክልሉን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመሩ፤ የክልሉን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራዎችን ማጠናከር፤ በመደመር ዕሳቤና ዕሴት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን በማጎልበት በፅኑ የኅብረ-ብሔራዊነት መሰረት ላይ የተገነባ፤ በተደማሪ አቅም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚችል ክልል መገንባት ይገኙበታል፡፡ #ርዕሰመስተዳድርጽቤት"

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከ1 ቀን በፊት
Facebook post image 1 Facebook post image 2 Facebook post image 3
Facebook post image 4
+8

"ጤና ጣቢያው ለማህበረሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ ዲላ፡መስከረም፣22/2019 ዓ.ም በዲላ ከተማ አስተዳደር የስሶታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያው የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ፎረም መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጅግሶ ጤና ጣቢያው የማህበረሰብ ፎረም በጤና ጣቢያዎች እና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ግንኙነትን በመፍጠር፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ጥራትና ፍላጎት ለመገምገም የተዘጋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን ገልፀዋል ። በአገልግልት አሰጣጥ ዙሪያ የተሰጡት አስተያየት በመቀበል መሻሻሎች መኖራቸውን ጠቁመው በቀጣይነት ለማህበረሰቡ ጥራት ያለውን አገልግሎት እንዲሰጥ ምክርቤት የድጋፍና ክትትል ስራዎችን እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት ያቀረቡት የስሶታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያው ዳይሬክተር ወይዘሮ አስቴር ጀቦ ከዲላ ዙሪያ ወረዳ ወደ ዲላ ከተማ አስተዳደር መመለሳቸው በጤና ጣቢያው ከፍተኛ ለውጥ መመዝገባቸውን አንስተዋል። በተለይም መድኃኒት አቅርቦት የማህበረሰብ ፍላጎት ያሟላ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ አስቴር አድስ አልትራሳውንድ ማሽን መግዛታቸውን አብራርተዋል። የጤና ጣቢያው ለማህበረሰብ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰሩ መሆናቸው ጠቁመው ከፎረሙ የሚገኙ ሀሳቦችን በየደረጃው የሚገኙ ፈጻሚዎች በመያዝ በሁሉም ዘርፍ የተጠናከሩ ስራዎችን በጋራ ተናቦና ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ጤና ጣቢያው በሁሉም ዘርፎች የታዩ ጉድለቶችን በማረምና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በማሻሻል የተገልጋዩን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እያከናወነ ባለው ተግባር አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል። መንግስት የማህበረሰብ ጤናን ለመጠበቅ ልዩ በመስጠት እየሰራ መሆኑን የገለፁት የስሶታ ቀበሌ አስተዳደር አቶ ደሳለኝ ካሳዬ ናቸው። የመድኃኒት ክፍል ባለሙያዎች የሆኑት መስፍን ዘለቀና ስስተር ትንሳኤ መራሳ በበኩላቸው ጤና አጠባበቅ ጣቢያው ወደ ዲላ ከተማ አስተዳደር ከተመለሰ በኃላ የማህበረሰብ ፍላጎት የሚያሟላ የመድኃኒት አቅርቦት መኖራቸውን ተናግረዋል። በፎረሙ ጤና ጣቢያ አገልግሎት አሰጣጥ፣ህብረተሰቡ በጤና ጣቢያው ላይ በሚስተዋሉ ጉዳዮችና በቀጣይ ከችግሮቹ በመላቀቅ ወደተሻለ ደረጃ መድረስ በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ ውይይቱ ተደርጓል። ተሳታፊዎች ጤና አጠባበቅ ጣቢያው ወደ ዲላ መመለሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በርካታ መሻሻሎች እንዳለው ተናግረዋል። በቀጣይ ጠንካራ አፈጻጸም አጠናክሮ በማስቀጠል ክፍተቶችን መቅረፍ እንደሚገባ ተገልጿል። መድረኩ በቀጣይነት መሻሻል ይገባቸዋል ያላቸው ነጥቦች ላይ ሃሳብና አስተያየት ቀርቦ ምላሽና ማብራሪያ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ፎረሙ መጠናቀቃቸውን የከተማው መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መረጃ ያመላክታል። ዘገባው፦በወንድሙ ክጴ ምስል፦በአቤነዘር ስዩም"

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከ1 ቀን በፊት
Facebook post image 1 Facebook post image 2 Facebook post image 3
Facebook post image 4
+8

"የትምህርት ስብራት ለመጠገንና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ ዲላ፡መስከረም፣22/2019 ዓ.ም የዲላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2019 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላ ሂደትና 1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ ክንውን ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የዲላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ተፈራ እንደገለጹት ትምህርት የሁሉ ነገር መሠረት የሆነ የእውቀት ስብስብ ያለበት ተቋም ነዉ ብለዋል። ከውጤት ስብራት ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ ክፍተቶችን በመቅረፍ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ መንግስት የሪፎርም ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። በየግዜው የመምህራን አቅም ለመገንባት ከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። የዲላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ግርማ ዶር (ዶ/ር) እንደገለጹት መንግስት 2030 የትምህርት ስርዓትን ወደ ዲጅታል ስማርት ለመለወጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ምዘና የትምህርት ቀዳሚ ተግባር በመሆኑ የትምህርት አመራር የተሻለና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የትምህርት ሥራ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ሂደታዊ ነዉ ያሉት ዶክተር ግርማ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል። በክረምት የንቅናቄ ተግባራትንና ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎች ምቹና ሳቢ ለማድረግ ሥራዎችን ተቀናጅተው በመስራት ውጤት መመዝገቡን የገለፁት የመምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡዊዩ ሀይሉ ናቸው የትምህርት መዋቅር ከተማሪዎች ወላጆች ጋር በ2018 ትምህርት ዘመን ውጤትና 2019 ትምህርት ዘመን አጀማመር ላይ መወያየት እንዳለባቸው አክለዋል። በ2019 ዓ.ም የተማሪ ቅበላ አፈፃፀም 96.4 ላይ መሆኑንና የትምህርት አጀማመር በተሻለ እንደነበርም ከሪፖርቱ ለማወቅ ተችሏል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በትምህርት ዘመኑ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን የከተማው መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መረጃ ያመላክታል። ዘገባው፦በወንድሙ ክጴ ምስል፦በአቤነዘር ስዩም"

የዲላ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከ1 ቀን በፊት
Facebook post image

"አቶ ተወልደ ተስፋዬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ጊዜ !"

የኢንቨስትመንት እድሎች

በዲላ ከተማ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች

በዘርፉ ያሉ እድሎች

አገልገሎቶች

ቅድሚያ የተሰጠው ዘርፍ

እንዱስትሪዎች

ግብርና

ማኑፋክቸሪንግ

ኑ አብረን ከተማዋን እናልማ!

  • ፈጣን አገልግሎት
ሴክተሮች

መምሪያዎች

የዲላ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መ/ቤቶችና ሥራና ኃላፊነት

ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት

ማዘጋጃ ቤታችን የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጥራት ለማሻሻል፣ ጽዱና ለሚኖሩባት ምቹ የሆነች ከተማ ለመፍጠር የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መሠረተ-ልማታዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የፕላን መረጃ መስጠት፡መሬቱ ለምን አይነት አገልግሎት (ለቤት፣ ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ...) እንደሚ...
ዝርዝር ይመልከቱ

የመሬት አስተዳደር መምሪያ

መምሪያው በከተማ የሚገኘውን የከተማና የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን በበላይነት የማስተዳደርና የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት። በዚህም መሠረት፡-  የከተማ አጠቃላይ የመሬት ካዳስተር ሥርዓት በማዘመን ለዜጎች የይዞታ ማረጋገጫና የባለቤትነት መብት ሰነድ በቀልጣፋና በተመጣጣኝ ዋ...
ዝርዝር ይመልከቱ

የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ

መምሪያው በከተማ የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገትን በማምራት፣ በማበረታታትና በመቆጣጠር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በዚህም መሠረት፡-  ቀልጣፋና ግልጽ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት በመስጠት ሕጋዊ የንግድ አካላት እንዲቋቋሙና እንዲስፋፉ ያደርጋል፤  በከተማ ውስጥ...
ዝርዝር ይመልከቱ

የቱሪዝም መምሪያ

መምሪያው የዲላ ከተማን በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ይተጋል። በዚህም መሠረት፡-  የከተማዉን የቱሪዝም ሀብቶች (ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ) በመለየት ካርታ በማዘጋጀትና በማስተዋወቅ ለቱሪስቶች ማራኪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ በከተማ ው...
ዝርዝር ይመልከቱ

የሥራና ክህሎት መምሪያ

መምሪያው በከተማ ውስጥ ምርታማ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የሰው ኃይልን ብቃት በማሳደግ ረገድ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታል። በዚህም መሠረት፡-  የከተማ የሥራ ገበያ ፍላጎት በማጥናት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚሰጠው ሥልጠና ከገበያ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ያደርጋል፤  የሥራ አጦችን...
ዝርዝር ይመልከቱ

የፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ

መምሪያው የከተማን የበጀት አዘገጃጀት፣ አፈጻጸምና ቁጥጥር በበላይነት የሚመራ ከፍተኛ አካል ነው። በዚህም መሠረት፡-  የከተማ ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በማቅረብ ሲፀድቅም አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ከክልል ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር የከተማ የገንዘብ...
ዝርዝር ይመልከቱ

የገቢዎች መምሪያ

መምሪያው በከተማ የሚገኙ የተለያዩ የመንግሥት ገቢዎችን በመሰብሰብና በማስተዳደር ረገድ ወሳኝ ኃላፊነት አለበት። በዚህም መሠረት፡-  በከተማ ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸውን የክልል ታክስና ግብሮች (እንደ በጀት ዓመታዊ ታክስ፣ የንብረት ታክስ፣ ወዘተ) በመለየት በሥርዓት መሰብሰባቸውን...
ዝርዝር ይመልከቱ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ

መምሪያው በከተማ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋትና የፈጠራ ሥራዎችን በማበረታታት ረገድ ያተኩራል። በዚህም መሠረት፡-  በከተማ የሚገኙ መምሪያዎችና የበታች አስተዳደሮች የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) አጠቃቀም አቅም እንዲያድግ ድጋፍና ሥልጠና ይሰጣል፤  የከተማ አ...
ዝርዝር ይመልከቱ

ኮርደር ልማት

እንደ ሐገር በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ጭምር እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ቀድሞ የነበሩ ከተሞችን ገፅታ በመቀየር አዲስ ገፅታን በማላበስ ከተሞችን ውብ ማራኪና ተመራጭ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡

የኮሪደር ልማት አዲስ ኢንሼቲቭ እንደመሆኑ በአተገባበር ወቅት ዉስን ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም አሁን ላይ በመንግስት ብቻ ሳይሆን በሕብረተሰቡ ተሳትፎም ጭምር ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል

ይህ አዲስ ከተማ ፈጣሪ ኢንሼቲቭዲላ ከተማን ለነዋሪዎች ለኑሮ ምቹ እንዲሁም ተወዳደሪ ከተማ ለማድረግ እየተተገበሩ ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች የመንገድ ኮሪደር ልማት መከወን ነው።

ባለፉት ዓመታት በከተማችን የመንገድ ኮሪደር ልማት የሚከወንባቸው በቁጥር 8 ዋና ዋና ኮሪደሮችን 18 ኪ.ሜትር በላይ በመለየት የፕላን ማስጠበቅ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡

ለኮሪደር ልማት ሥራ የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የከተማ ፕላን የማስጠበቅ ሥራ ሲሆን በዚህመ ረገድ በከተማው ነዋሪ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም በየደረጃው ባሉ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ሥራ ከ19.2 ኪሎሜትር በላይ ፕላን የማስጠበቅ ተግባር ተከናውኗል፡፡

የከተማው ነዎሪዎች በፕላን ማስጠበቅ ተግባሩ ባደረጉት ንቁ ተሳትፎ ከመንግሥት ሊወጣ የነበረውን 654 ሚሊዮን ብር ማዳን የተቻለ ሲሆን 517 ቤቶችን በማፍረስ የከተማ ፕላን ማሰጠበቅ ተግባር በማከናወን ለቀጣይ የመንገድ ኮሪደር ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡

ከአዲስ አበባ ሞጆ ኢትዮ ኬኒያ የሚዘልቀው አስፋልት መንገድ አቋርጧት የሚያልፈው  የዲላ ከተማመግቢያበር ላይ እጅግ ሳቢና ማራኪ የመግቢያ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ በከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በኮሪደር ልማት በመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት 16 ሺህ 700ካሬሜትርተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በተመሳሳይ 8.4 Km እግረኛመንገድ ተጠናቋል፡፡

በቁጥር 5 እስናክሀውስግንባታ ተጠናቅቆ በእዚሁአከባቢ 20 ማረፊያ መቀመጫዎች ተዘጋጅተ ሕብረተሰቡ አረፍ ብሎ ነፋሻ አየር እንዲቀበልና ራሱን እንዲያዝናና አስተዋኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

በከተማው የሚገኙ 2 አደባባዮችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማልማት እና የማስዋብ ሥራ ተሰርቶ 4ኪ.ሜ የመንገድ መብራት ማስዋብ ሥራ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡.

የኮሪደር ልማት ከተማን እንደ አዲስ ከነፍጠር ባሻገር ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል በመፍጠርም አበርክቶቱ ከፍተኛ ሆኖ በዲላ ለ1ሺህ 205 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

 

የዲላ ከተማ የኮሪደር ልማትን በማስቀጠል በከተማዋ ክልል ዋና ዋና መንገዶች ላይና አደባባዮች ብሎም ሰው ሰራሽ ሐይቅም ጭምር  በመስራት አዲስ ከተማ የመፍጠሩ ተግባር ከነዋሪዎቻችን ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ኮርደር ልማት
ኮርደር ልማት
ኮርደር ልማት
ኮርደር ልማት
ኮርደር ልማት
ኮርደር ልማት
ኮርደር ልማት

ዲላ በለውጥ ምዕራፍ ላይ ናት!

እንኳን ወደ ዲላ ከተማ አስተዳደር ይፋዊ የድረ-ገጽ መረጃ ቋት በሰላም መጣችሁ!

የከተማችን አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ዋነኛ ዓላማ በመንግስትና በህዝብ መካከል የታመነ ድልድይ በመሆን፣ የዲላን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ለነዋሪዎቻችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ ነው።

ዲላ በለውጥ ምዕራፍ ላይ ናት!

በአሁኑ ወቅት በከተማችን በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የሚከናወኑ፦

  • የኮሪደር ልማት ስራዎች፣
  • የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታ እና
  • ሌሎች ግዙፍ የመሠረተ ልማት ስኬቶች የከተማችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎቻችን ምቹ የኑሮ ሁኔታን እየፈጠሩ ይገኛሉ።

የዲጂታል ሚናችንና ግባችን፦

  1. ወቅታዊ መረጃ፦ የልማት ስራዎችንና የመንግስት ውሳኔዎችን በታማኝነት ማጋራት።
  2. የመረጃ ሉዓላዊነት፦ በከተማችን ሰላምና ልማት ላይ የሚነዙ የተዛቡ መረጃዎችን (Misinformation) በእውነተኛ መረጃ መመከት።
  3. ሁለትዮሽ ግንኙነት፦ የመንግስትን ድምፅ ማስተማር ብቻ ሳይሆን፣ የህዝቡን ቅሬታና ጥቆማ የምንቀበልበት ክፍት መድረክ መሆን።

የክብር ጥሪ፦

የዲላ ከተማ ነዋሪዎችና የከተማችን ወዳጆች በሙሉ፤ ይህንን ድረ-ገጽ እንደ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ በመጠቀም ለከተማችን ዕድገትና ሰላም ገንቢ አስተያየታችሁን እንድታካፍሉን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

መረጃ የልማት መነሻ ነው!

 

ዲላ በለውጥ ምዕራፍ ላይ ናት!

የፎቶግራፍ አምዶች

የከተማችንን ውበት ያስሱ